ርችት መተኮስ ክልክል ነው – ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓልን ሰበብ በማድረግ በማንኛውም ሁኔታ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በሕገወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ የሚያዘዋውሩ አካላት በዓላትን ጠብቀው ርችትን ሽፋን በማድረግ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን እንደሚተኩሱ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በዚህም ቀደም ሲል ጉዳት ያደረሱ አደጋዎች ማጋጠማቸውን እና ለህብረተሰቡ ደኅነንት ሲባል ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡም ርችት ባለመተኮስ እንዲተባበር እና ይህን ክልከላ የተላለፉ ሲያጋጥመው ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል፡፡