የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል- የድሬዳዋ ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል በፍጹም ሰላም እንዲከበር የአስተዳደሩ ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት እና ለውጥ ሥራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ፖሊስ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ከሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ዛሬ ጠዋት ለጸጥታ ኃይሉ መመሪያ መሰጠቱን እና ይህን ተከትሎም ወደ ስምሪት መገባቱን ነው ያረጋገጡት፡፡
ወንጀልን ለመከላከል ከጸጥታ ኃይሉ ዝግጅት በተጨማሪ የሕብረተሰቡ ሚና የጎላ በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪ እንደተለመደው ሁሉ ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከትም በነጻ የስልክ መስመር 620 ላይ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሶማሊኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡
በተጨማሪም በቀጥታ የስልክ መስመሮች 0251-111-600 እና በ0251-115-211 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ነው ኮማንደር ገመቹ የገለጹት፡፡
የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ አስተማማኝ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበው÷ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!