Fana: At a Speed of Life!

ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሊቱን ሙቀትን ጨምሮ የቫይረሱን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት የወጡ መረጃዎችም ቦሪስ ጆንሰን በግል ዶክተራቸው የቀረበውን ምክረ ሃሳብ ተከትሎ ለክትትልና ህክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ያመላክታሉ።

ሆስፒታል ከገቡ በኋላም በህክምና ባለሙያዎች ምርመራ እና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጋርዲያን አስነብቧል።

ቦሪስ ጆንሰን ከ10 ቀን በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ራሳቸውን አግልለው መቆየታቸውም የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ ጋርዲያን እና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.