Fana: At a Speed of Life!

የወጪንግድን ለማሳደግ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የወጪ ንግዷን ለማሳደግ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የንግድ ግንኙነቷን እያጠናከረች መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የዓለም ዓቀፍና ቀጣናዊ ትስስር ስራ አስፈጻሚ ሙሴ ምንዳዬ  እንደገለጹት÷ ጎረቤት ሀገራት ጋር በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በጥራጥሬ ምርቶች የሚደረገው የንግድ ግንኙነት ትልቅ እመርታን እያሳየ ነው።

ከጎረቤት ሀገራት ባለፈም ከእስያ ሀገራት ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት 45 በመቶ የደረሰ ሲሆን÷ የአውሮፓ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያ ምርቶች መዳረሻ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአጎዋ እድል ብትሰረዝም የአውሮፓና የቻይና ሀገራት የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ፈቃድ በመስጠታቸው ዕድሉን ለመጠቀም ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣይ ከችሮታ ገበያዎች በመውጣት አቅሟን ከሚመጥኑ ሀገራት ጋር የንግድ ስምምነቶችን በማድረግ የገበያ መዳረሻዎቿን አስተማማኝ ለማድረግ ጥረት እያደረገች መሆኑ አስረድተዋል ፡፡

ዘርፉን እየፈተነ ያለውን የኮንትሮባንድ ንግድ ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በድንበር አካባቢዎች የሚዛን ቁጥጥር በማድረግ የድንበር ኮታዎችን የሚወሰን አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ለማሳደግ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና የግብይት ሰንሰለቶችን ማዘመን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩየኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ለማሳደግ ቴክኖሎጅዎችን መጠቀም እና የግብይት ሰንሰለቶችን ማዘመን እንደሚገባም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል ፡፡

መሳፍንት እያዩ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.