Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ተወካይና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ተወካይና ዳይሬክተር ማዊራ ቺቲማ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ድጋፍ በተከናወኑ ስራዎች እና በተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በቀጣይ በመስኖ ልማት፥ በገበያ ትስስርና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራትም ተወይያተዋል።

በውይይቱ ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ውሃን በሰፊው ለልማት ለማዋል በሚደረገው ሂደት በመስኖ ልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል።

ከሚታረሰው 14 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ 7 ሚሊየን ሄክታር በአሲድ የተጠቃ መሆኑ አሳሳቢ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ በአፈር ለምነትና ጤንነት ላይ እንሰራለን ብለዋል።

በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት የማዳበሪያ ዋጋ ሶስት እጥፍ ስለጨመረ በቀጣይ በኮምፖስት ዝግጅት ላይ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ በአነስተኛ መስኖ ልማት ፣ የአርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር እና የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.