Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍፍል መፍትሄ የሚሻ የታዳጊ ሀገራት ፈተና መሆኑን አስገነዘበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍፍል የታዳጊ ሀገራት ፈተና በመሆኑ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ስትል በዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ላይ አስገነዘበች።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ ዓሊ በታዳጊ ሀገራት በፆታ፣ በቋንቋ፣ በዲጂታል ክኅሎት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ በአካባቢ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዕቃዎች እና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ገደቦችና ክፍፍሎች እንደሚታዩ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያም በመድረኩ ጉዳዩ የጉባዔው አንድ አጀንዳ ሆኖ ምክክር እንዲደረግበትእና ዕልባት እንዲሰጠው ጠይቃለች።

ጉባዔውም ይህንኑ ተቀብሎ የዲጂታል ክፍፍል የ2023 ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ አንዱ የመወያያ አጀንዳ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

18ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔ በቀጣይ ዓመት በጃፓን ይካሄዳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.