Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በልጧል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በልጧል።

434 ሺህ 703 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

እንደ ጆን ሆፕኪንሰ ዩኒቨርሲቲ መረጃ 114 ሺህ 331 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።

በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 557 ሺህ 590 የደረሰ ሲሆን ይህም ዓለም ላይ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

በስፔን 166 ሺህ 831፣ በጣሊያን 156 ሺህ 363፣ በፈረንሳይ 133 ሺህ 607 እና በጀርመን 127 ሺህ 854 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በዓለም የሟቾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን ጣሊያን 19 ሺህ 899 ዜጎቿን አጥታለች።

በስፔን 17 ሺህ 209፣ በፈረንሳይ 14 ሺህ 393፣ በብሪታኒያ 10 ሺህ 612 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በአፍሪካ 14 ሺህ 400 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 788 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

2 ሺህ 823 ሰዎች ደግሞ ከከቫይረሱ አገግመዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.