Fana: At a Speed of Life!

“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በማንበብ ከሚገኘው ጥቅም በተጨማሪ ሕብረተሰቡ በልማት እንዲሳተፍ ዕድል መፍጠሩ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በማንበብ ከሚገኘው ጥቅም በተጨማሪ ሕብረተሰቡ ለሀገሩ ልማት ተሳታፊ የሚሆንበትን ምቹ ዕድል መፍጠሩን ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የቱሪዝም ልማትን ለማሳለጥ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈው “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ መጽሐፉን በማንበብ ከሚገኘው ጥቅም በተጨማሪ ሕብረተሰቡ ለሀገሩ ልማት ተሳታፊ የሚሆንበትን ምቹ ዕድል በመፍጠር ሌላ ፋይዳ አለው፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ መዳረሻዎች እንዲለሙ መታሰቡን ብሎም ባህላዊ እና የተፈጥሮ ሃብቶችን ያማከለ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በታሰበው ልክ ለምተው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ከዚህ በፊት በዘርፉ የተከናወኑ አፈጻጸሞች ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

በመጽሐፉ ሽያጭ የሚገነቡ፣ የሚለሙና የሚታደሱ መዳረሻዎች ለሀገር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡

በሌላ ዕቅድ ቢሆን መዳረሻዎቹን ለማልማት በርካታ ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ጠቅሰው÷ በመጽሐፉ ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሃብት ተሰባስቦና ለምተው የተሻለ ገቢ እንዲያስገኙ መመቻቸቱ ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ትሩፋት መሆኑንም ነው የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጽሐፋቸውን ሽያጭ ገቢ ለቱሪዝሙ ኢንዱስትሪ ማድረጋቸው ዘርፉን ለማሳደግ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በኢትዮጵያ ያልለሙ የቱሪዝም ሃብቶችን ወደ ገበያና ልማት ለማምጣት ዓይነተኛ መንገድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ክልሎች መጽሐፍቱን በመሸጥ ገቢው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በንቃት እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ መንግስት በቁርጠኝት እንደሀገር የቱሪዝም መዳረሻዎችን እያለማ መሆኑን ገልጸው÷ ለዚህም የገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ለአብነት አንስተዋል።

ፕሮጀክቶቹ ለጎብኚ ተጨማሪ መዳረሻ በመሆን በመስኅብነት እያገለገሉ መሆናቸው እና በሥራ ዕድል ፈጠራም የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በቱሪዝሙ ዘርፍ የተያዘውን የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በማገናዘብ በርካታ ጎብኚዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችሉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መዳረሻዎች እንዲኖሩ የፕሮጀክቶቹ እገዛ ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.