የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያ የቻይና በረራውን የካቲት 14 ቀን 1965 ዓ.ም ወደ ሻንጋይ ከተማ በማድረግ አገልግሎቱን መጀመሩን አስታውሷል፡፡
ከጥቅምት 28 ቀን 1966 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ መዳረሻውን ወደ ቤጂንግ ከተማ በመቀየር አገልግሎን መቀጠሉንም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ5 የመንገደኛ እና በ9 የዕቃ ጭነት መደበኛ በረራዎች አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 66 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ 10 የቻይና ከተሞች እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
መዳረሻዎቹም ቤጂንግ፣ ጓንዡ፣ ሼንጁ፣ሻንጋይ፣ ሸንዘን ፣ ውሀን፣ ቻንግሻ፣ ዢያመን፣ ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ መሆናቸውንም አየር መንገዱ ጠቁሟል፡፡