Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝን ሹመት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዛህራ ኡመር አሊ ሹመትን መርምሮ አፀደቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው 13ኛ መደበኛ ጉባዔ በዕጩነት የቀረቡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዛህራ ኡመር አሊ ሹመትን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ  እና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዛህራ ኡመር አሊ ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ በመምራት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቋል፡፡

በየሻምበል ምህረት

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.