Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በተመድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ ጋር ተወያይተዋል።
 
በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች እና መንግስት ከተመድ እና ኤጄንሲዎቹ ጋር የሚያደርገውን ትብብር ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት አስረድተዋል።
 
ከሰላም ስምምነቱ ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያም መንግስት ብሄራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትህ፣ ብሄራዊ ዕርቅ እና በተጎዱ አካባቢዎች የተሃድሶ እና የመልሶ ግንባታ ለማካሄድ ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
 
አቶ ደመቀ አያይዘውም ለጋሽ እና የተመድ ኤጄንሲዎች መንግስት እያደረገ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ካትሪን ሶዚ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ ለደረሰው የሰላም ስምምነት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.