በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
በዚህም 9 ሰዓት ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድንን ሁለቱንም ጎሎች ብሩክ ሙሉጌታ ሲያስቆጥር የወላይታ ዲቻን ጎሎች ቃልኪዳን ዘላለምና ዮናታን ኤልያስ አስቆጥረዋል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ መቻልን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግብ ሽመክት ጉግሳ አስቆጥሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!