Fana: At a Speed of Life!

በታላቁ አንዋር መስጅድ የረመዷን ወር የ27ኛው ሌሊት የተርሃዊ ሰላት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ አንዋር መስጅድ የረመዷን ወር የ27ኛው ሌሊት የተርሃዊ ሰላት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በታላቁ የረመዷን ወር ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት 7ኛው ጾሙ፣ በተጀመረ በ27ኛው ሌሊት የሚደረገው የተርሃዊ ሰላት ህዝበ ሙስሊሙ በጉጉት የሚጠበቀው ነው።

በረመዷን ወር 27ኛው ሌሊት “ለይለቱል ቀድር” ህዝበ ሙስሊሙ ሌሊቱን የሚያሳልፈው ለረጅም ሰዓታት በጸሎት  የአላህን ይቅርታ እና ምህረትን አብዝቶ  በመለመን ነው፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.