Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩ ተመለከተ፡፡

በዚህም ሥራ አቁመው የነበሩ ፋብሪካዎች ጭምር ወደ ሥራ እንዲመለሱ ማድረግ ያስቻለ ውጤት መገኘቱ ነው የተገለጸው፡፡

የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ግምገማ እና የምክክር መድረክ በጅግጅጋ እየተካሔደ ነው፡፡

መድረኩ እየተካሄደ የሚገኘው÷ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደርና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው፡፡

አቶ ሙስጠፌ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢንዱስትሪ ለአንድ ሀገር ዕድገት ወሳኝ ከሆኑ ዘርፎች ግንባር ቀደሙ ነው ብለዋል፡፡

በሶማሌ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ትኩረት እንዳልተሰጠው ጠቁመው÷ ለዚህም የኢንቨስትመንት ስበት ማነስ እና ሌሎች ጉዳዮችን በምክንያትነት አንስተዋል።

በቀጣይም በክልሉ ምርቶችን ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ ለወደብ ያለውን ቅርበት ግምት ውስጥ ያስገባ የልማት ሥራ ይካሄዳል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ መላኩ በበኩላቸው÷ አንድ አይነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ለሀገር ቀጣይነት ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጠንካራ ትስስር ያለው የኢኮኖሚ ስርዓት በመፍጠር ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪው በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.