የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የቀብር ሥነ ስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
በቀብር ሥነ ስርዓቱ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እንዲሁም የአርቲስቱ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል።
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በ1949 ዓ.ም በነቀምቴ ከተማ የተወለደ ሲሆን÷በጥበቡ ዓለም ለ48 ዓመታት ያህል ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል።
አርቲስቱ በኦሮምኛ ቋንቋ በርካታ ሥራዎችን ለሕዝብ በማድረስ አድናቆትና ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህንድ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
በፍቅረሚካኤል ዘየደ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!