የኢትዮጵያ ከንቲባዎች ፎረም የፊታችን ሚያዚያ 21 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከንቲባዎች ፎረም ከፊታችን ሚያዚያ 21 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሰጡት መግለጫ÷ፎረሙ ከተሞች ያላቸውን ልምድ የሚጋሩበት እና የልምድ ልውውጥ የሚያካሄዱበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ጥናታዊ ጽሑፎችን ጨምሮ አዳዲስ ሃሳቦች የሚቀርቡበት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ÷የኢትዮጵያ ከተሞችን የእህትማማችነት ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል፡፡
በፎረሙ የመጨረሻ ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተሞች በሁለንተናዊ መልኩ ራሳቸውን በሚያሳድጉበት አግባብ ላይ የስራ መመሪያ እንደሚሰጡ ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ ከ300 በላይ ከንቲባዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡
በወንድሙ አዱኛ