ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቶ ግርማ የሺጥላ መሰዋት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሀዘን መግለጫቸው÷በወንድማችን ግርማ የሺጥላ መሰዋት እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡
ግርማ ላመነበት የወንድማማችነት እና ህብረብሔራዊ አንድነት አላማ በጀግንነት የታገለ የአቋም ሰው ነው ሲሉም አውስተዋል።
ዛሬ ግርማን መግደል ብትችሉም ሀሳቡንና የቆመለትን አላማ መግደል አትችሉም፤ የጽንፈኝነት ተሸናፊ ሀሳብ እየሞተ የወንድማማችነት ሀሳብ አሸናፊ ሆኖ ይቀጥላል ነው ያሉት።
“ለቤተሰቦቹ ፣ለወዳጆቹ እና ለስራ ጓዶቹ መጽናናትን እየተመኘሁ፤ ፈጣሪ ነብሱን በአፀደ ገነት ያሳርፈው” ሲሉም ገልጸዋል።