Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

የክልሉ መንግስት በሃዘን መግለጫው ÷ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ በተጋች ቁጥር ዘመን ያለፈበትን የጽንፈኝነት መንገድን መርጠው በግርማ የሺጥላ ልብ ሠባሪ ጥቃት በፈጽሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብሏል።

የእነዚህ ኃይሎች ዓላማ ሀገር የማፍረስ እና ግልጽ ሽብር በመፍጠር የህዝቦች አብሮነት እንዲሸረሸር የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም  ሊታገላቸው እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዘው የክልሉ መንግስት÷የሀሳብ ሜዳ በሠፋበት በዚህ ወቅት ጽንፈኝነት የመረጡ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንደሚወጣ ያረጋግጣል ብሏል።

የክልሉ መንግስት በአቶ ግርማ የሺጥላ በደረሰው ድንገተኛ ህልፈት የተሠማውን ሀዘን ገልጾ÷ ክልሉ ለቤተሰቦቻቸውና እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብም መጽናናትን ተመኝቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.