Fana: At a Speed of Life!

ሩዋንዳ የኮሮና  ቫይረስ ወረርሽኝ እያከተመ መምጣቱን ተከትሎ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋ እመርታ አሳየ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩዋንዳ የኮሮና  ቫይረስ ወረርሽኝ እያከተመ መምጣቱን ተከትሎ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋ እመርታ አሳይቷል፡፡

ሀገሪቱ ከአንድ ዓመት በፊት ከዘርፉ ያገኘችው ዓመታዊ ገቢ ቀድሞ ከነበረው በሦስት እጥፍ ቀንሶ ወደ 164 ሚሊየን ዶላር ወርዶ ነበር፡፡

ይሁንና ተከትሎ በመጣው  2022 የገቢ መጠኑ እንደገና በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ሀገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፍ 445 ሚሊየን ዶላር አግኝታለች መባሉን የሩዋንዳው ዘ ኒው ታይምስ ዘግቧል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥም ሩዋንዳን ከጎበኙ ከ1 ሚሊየን በላይ ቱሪስቶች መካከል 60 በመቶው ከአፍሪካ መሆናቸው የአህጉሪቱ ህዝቦች የእርስ በርስ ትስስር ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አመላክቷል፡፡

ሩዋንዳ ባለፈው ዓመት ከዓለም ምርጥ 50 የቱሪዝም መዳረሻ ሀገራት አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ይኸውም በሜሪካው ታይም መፅሔት መሥፈርት ተመርጣ አምና ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.