Fana: At a Speed of Life!

ግል ትምህርት ቤቶች ያደረጉት ጭማሪ የተጋነነ ነው ሲሉ  ወላጆች ቅሬታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ትምህርት ቤቶች ያደረጉት ጭማሪ ከመክፈል  አቅማችን በላይ የተጋነነ ነው ሲሉ  ወላጆች ቅሬታቸውን ገለጸዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ትውልድን በእውቀት እና በስነምግባር ማነጽ ግባቸው ቢሆንም÷ እንደ ንግድ በድርድር እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ አቤቱታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡ ወላጆች ተናግረዋል።

ስርዓተ ትምህርት ባለሞያው ተባባሪ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተክለማርያም፣ የግል ትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ በመማር ማስተማሩ እና በትምህርት ጥራት ላይ የራሱ  የሆነ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡

ጭማሪው በወላጆች ላይ ከፍተኛ  ጫና ስለሚያሳድር ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ከትምህርት ገበታ በማስቀረት ማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ሊያደርግ እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ዶክተር መኮንን ካሳሁን በበኩላቸው÷  መንግስት ዋጋ ማውጣት እና መተመን ባይችልም ቁጥጥር ማድረግ  እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።

ምሁራኑ÷  መንግስት በራሱ ትምህርት ቤቶች ጠንክሮ ቢሰራ እና የግል ትምህርት ቤቶችን  ቢደግፍ  ችግሩ  ሊቀረፍ እንደሚችልም  መክረዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.