Fana: At a Speed of Life!

ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ  “የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ”ን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ “ከቤት-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ቃል የተሰናዳውን “የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ”ን ጎበኙ።

በጉብኝቱም ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊች፣ አባገዳዎች እና ሞዴል አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

የሀገሪቷ የግብርና አሰራር ስርዓት ያስቀመጠውን አሻራ ማሳየትና በዲጂታል አብዮት የግብርናውን ትግበራ አቅጣጫ ማሳየት የአውደ ርዕዩ ግብ ነው ተብሏል።

በአውደ ርዕዩ በግብርናው መስክ የተሰማሩ ከ70 በላይ የምርምርና ፈጠራ ስራዎች፣ ዲጅታላይዜሽን ግብርና እና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በግብርናው ዘርፍ ለተሰማሩ ተዋንያን፣ ባለድርሻና አጋር አካላት በሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ አሰራሮችን እና ልምዶችን ለማዳበር መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የተጀመረው የሜካናይዜሽን የግብርና ስራ ይበልጥ እንዲጎለብት የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል።

በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን አውደ ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም መክፈታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.