Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 2ኛ ዙር የበልግ አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ54 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የሚተከሉበት ሁለተኛ ዙር የበልግ አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።

መርሐ ግብሩን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ በፋኒቃ ቀበሌ አስጀምረዋል።

በክልሉ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከ54 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በበልግ ወቅት ይተከላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ2015 ዓ.ም በበልግና የክረምት ወራት ከ180 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ እንደሚቀጥል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ማስጀመር ጎን ለጎን በገበታ ለትውልድ ከሚለሙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን የደንቢ ፏፏቴና ሰው ሰራሽ ሐይቅ አቶ አደም ፋራህና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.