Fana: At a Speed of Life!

የተጀመረው የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመረው የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

“የደምበኞች ደኅንነት በዲጅታል ኢኮኖሚው” በሚል መሪ ቃል “ኤፍ. ኤስ. ዲ” ኢትዮጵያ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷ለደምበኞች ሚዛናዊ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት ለመሥጠት የዲጅታል ግብይት ሥርዓቱን ማስፋት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዲጂታል ግብይት ሥርዓቱ አዋጅ እና መመሪያዎች ወጥተው ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ነው ያስታወሱት፡፡

አሁን ላይ የሥርዓቱ ፈር መያዝ በ2025 ዲጅታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጀመረውን ጉዞ የተቃና ያደርግልናል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ።

በመርሐ-ግብሩ ደንበኞች በዲጅታል ኢኮኖሚው ውስጥ ግብይቶችን ሲፈፅሙ ለሌቦች እና አታላዮች ሳይጋለጡ እንዲገበያዩ የሚያስችሉ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራት እና ድርጅቶች ጋርም የልምድ ልውውጦች ተደርገዋል።

በትዕግስት አስማማው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.