Fana: At a Speed of Life!

ከኮቪድ 19 ያገገሙ ሰዎች  ዳግም በቫይረሱ ስላለመያዛቸው  የተገኘ ማስረጃ የለም -የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 18፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ከኮቪድ 19 ያገገሙ ሰዎች  ዳግም በቫይረሱ ስላለመያዛቸው  የተገኘ ማስረጃ  አለመኖሩን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቀው÷ ከ ኮቪድ 19 ያገገሙ  ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ  ያዳበሩት ፀረ-ተህዋስያን ዳግም በኮሮቫቫይረስ ኢንፌክሽን  እንዳይጠቁ  ማድረግ መቻል አለመቻሉ “ምንም መረጃ የለም” ብሏል ፡፡

አንዳንድ መንግስታት “ለኮቪድ 19” መንስኤ የሆኑትን እንደ ለሳርስ(SARS) እና ኮቪድ 2(CoV-2 )የተባሉ ፀረ እንግዳ አካላትን በመመርመር ግለሰቦች እንደገና  በኮሮና ቫይረስ አይጠቁም የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁሟል፡፡

በዚህም ከበሽታው ነጻ የሚል ፓስፖርት ወይም ሰርተፊኬት እንዲያገኙ በማድረግ  ወደስራ  እንዲመለሱ  ወይም  እንዲጓዙ  ይፈቅዱላቸዋል ነው ያለው፡፡

እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ የቫይረሱን ስርጭትን  ሊጨምር እንደሚችልም አስጠንቅቋል።

ከዚያም ባለፈ ይህ  ዓይነቱ አሰራር  ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቫይረሱን  ለመከላከል የሚሰጠውን የቅድመ ጥንቃቄ  እርምጃዎችን  ችላ እንዲሉት ያደርጋቸዋል   ነው ያሉት።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ÷ መንግስታት  ከበሽታው ላገገሙ ሰዎች  ከየበሽታው ነጻ የሚል  ፓስፖርቶች  ወይም የምስክር ወረቀቶች  መስጠት እንደሌለባቸው አስጠንቅቆ  እንደዚህ አይነቱ እርምጃ ወረርሽኙ  በቀጣይ የመሰራጨት አደጋን ሊጨምር ይችላልም ብሏል ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ እና ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.