Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የተመራ ልዑክ ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል።

ልዑኩ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉለት አሚኮ ዘግቧል።

ሁለቱ ርዕሳነ መሥተዳድሮች በሁለቱ ክልል ሕዝቦች እና ቀጣይ የሠላም ጉዞ ዙሪያ ከባሕር ዳር ከተማ ከተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር መክረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)÷ ልዩነቶች ይኖራሉ ልዩነቶችን ግን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር መፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው÷የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ወደ ቀደመው ሁኔታው መመለስ አለበትም ነው ያሉት፡፡

ትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርበታል ያሉት ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)÷ተከባብረን እና ተደማምጠን ልዩነቶቻችን ለመፍታት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የፖለቲካ አመራሩ የጀመረውን የሠላም ግንኙነት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በተለይ ደግሞ አዋሳኝ አካባቢ ያሉ የሁለቱም ክልል ሕዝቦች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ርዕሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በበኩቸው÷ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው ብለዋል፡፡

“አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

“የሁከት እና ግርግር አጀንዳዎች የሚታያቸው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ለሕዝብ ካሰብን እና ከሠራን ከሠላም ውጭ የተሻለ አማራጭ የለንም”ብለዋል፡፡

#Ethiopia #Amhara #Tigray
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.