በቻይና የሚማሩ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን የቱሪዝም ሐብቶች አስተዋወቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ጂሊን ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን የባሕልና የቱሪዝም ሐብቶች ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ማስተዋወቃቸው ተገለጸ።
ተማሪዎቹ የሀገራቸውን የባሕልና የቱሪዝም ሐብቶች ያስተዋወቁት በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባባር ነው፡፡
ዝግጅታቸውን ያቀረቡት በዩኒቨርሲቲው ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በማስተዋወቂያ ዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያን ባሕላዊ ምግቦች፣ የቱሪዝም መስኅቦችና አጠቃላይ የኢትዮጵያን ታሪክ በተለያየ ዘዴ ማቅረብ ተችሏል፡፡