ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል – አምባሳደር መሐሙድ ዲሪር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ አጀንዳ ለማሰባሰብ ስለሚከናወኑ ተግባራትና የውይይት ተሳታፊዎች መረጣ ላይ ከሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ጋር በሐረር ከተማ እየመከረ ነው ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፥ ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል እንዲሁም በዜጎች እና መንግስት መካከል መተማመን እንዲኖር ያስችላል።
በዜጎች መካከል ግጭትን በውይይት በመፍታት ማህበራዊ ውልን ለማደስም ምክክሩ ሚናው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።
ምክክሩ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ልዩነቶችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡