Fana: At a Speed of Life!

የ2023 የአፍሪካ-እስያ ወጣቶች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 የአፍሪካ-እስያ ወጣቶች ፎረም “ጤናማና አቅም ያለው ወጣት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በኦየስ-ግሎባል ፋውንዴሽን አዘጋጅነት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካና እስያ አህጉር የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህባራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ፣ የአፍሪካና እስያ ሀገራት ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የመርሐ ግብሩ ዋና አላማ የአፍሪካና የእስያ ወጣቶች በስራ ፈጠራ፣ በጤና፣ በከባቢያዊ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላም፣ በበጎ ፈቃደኝነት እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች እውቀትና ልምድ እንዲጋሩ በማድረግ ወጣቶችን ለማብቃት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቶች በሀገራት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ቁልፍ ሚና ያላቸው መሆኑን አስተዋል።

በመሆኑም ወጣቶች በአመራር፣ በስራ ፈጠራ፣ በኢኮኖሚና ሰላም በማስፈን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ይህ መድረክ ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ቡሲራ ባስኑር በበኩላቸው፣ ወጣቶች የሀገራቱ ሁሉ የኢኮኖሚና ፓለቲካዊ ክዋኔ ማርሽ ቀያሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አፍሪካንና እስያን በወጣቱ ኃይል ተሳትፎ ማስተሳሰር በሁለቱ አህጉሮች መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.