Fana: At a Speed of Life!

የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአክሱም ሐውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመድኅን ፍፁም ብርሀን እንዳስታወቁት÷ በአክሱም ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት ተደርገዋል።

ቅርሶቹ ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ኅብረተሰቡ በጉልበቱ፣ በገንዘቡ እና በሙያው ያደረገው ተሳትፎ የላቀ እንደነበረም ተናግረዋል።

የቱሪዝሙን ዘርፍ ወደነበረበት ለመመለስ እና ኅብረተሰቡ ለቱሪስቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ለፎቶ አንሺዎች፣ አስተርጓሚዎች፣ ለባህላዊ ጌጣጌጦች እና ቅርፃቅርፅ ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለ ሆቴሎች ሥልጠና መሰጠቱን አሰረድተዋል።

በአክሱም እና አካባቢው የሚገኙ ቅርሶች እና ሙዚየም ለቱሪስቶች ተደራሽ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት መደረጋቸውን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአክሱም እና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለመጎብኘት እና ለማየት በየዓመቱ ከ30 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ይጎበኙት እንደነበር አስታውሰዋል።

ጎብኝዎቹ በአክሱም እና አካባቢ በሚኖራቸው ከ2 እስከ 3 ቀናት ቆይታ ከሚያገኙት አገልግሎት የቱሪዝም ፅህፈት ቤት እና ነዋሪው በዓመት ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ያገኝ እንደነበረም ጠቅሰዋል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.