Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ሲካሄድ የነበረው የስልጠና መድረክ ተጠናቋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ” መፍጠንና መፍጠር ፣ የወል እዉነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል አቅጣጫ” በሚል መሪ መልዕክት ከሰኔ 05 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉ የስልጠና መድረክ ተጠናቋል።

በአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር) በዚህ ጊዜ ፥ መድረኩ ውስጣዊ አንድነትን የሚያጎለብት፣ ቁጭት የፈጠረና የህዝብ ጥያቄዎችን መፍታት የሚያስችል መተማመን የተደረሰበት ሆኖ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

የአማራ ህዝብ ሰላም፣ ልማት፣ ውስጣዊ አንድነትና አብሮነትን ይፈልጋል ብለውም ፥ የህዝቡን ስነ-ልቦና የማይመጥን እንቅስቃሴና ድርጊት የሚፈፅሙ አካላትን መልክ የሚያስይዝ ዲሞክራሲያዊና ህጋዊ ስርዓትን የተከተለ ትግል ማድረግ እንደሚገባም ነው ያመላከቱት።

በተጨማሪም በአቶ ኦርዲን በድሪና ሌሎች አመራሮች መሪነት ሲካሄድ የቆየው የጋምቤላ ክልል የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ፥ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶች በማስቀጠልና ፈተናዎችን በድል በመሻገር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል ብለዋል።

በተለይም አሁን ላይ ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባናልም ሲሉ ነው ያሳሰቡት።

እንዲሁም ለተጀመረው የልማት ጉዞ መሰናክል የሆኑትን ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት አብሮ መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ጽ/ቤት ኃላፊ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው ፥ እንደብልጽግና ፓርቲ ግብርናንና ኢንዱስትሪን ጨምሮ እየተገበራቸው በሚገኙት አምስት የብዝሃ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ስራዎች በርካታ ስኬቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲካሄድ የቆየው መድረክ ተጠናቋል፡፡

በመድረኩም በቀጣይ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ፣ የአረንጓዴ አሻራን በማጠናከር፣ የግብርና ምርትና ምርታማነት እና የብልፅግና ፓርቲ በሌሎች ዘርፎች ያስቀመጣቸው ቁልፍ አቅጣጫዎችን ተግባራዊና ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የፓርቲው አመራሮች በቁርጠኝነት ሊረባረቡ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ተጠናቋል።

በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ እንደተናገሩት ፥ አመራሩ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት በማጠናከር ለስኬትና ለውጤት የሚሠራ ጠንካራ የአመራር መዋቅር እንዲዘረጋ በትጋት ሊንቀሳቀስ ይገባል።

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው እንደገለጹት ፥ በጊዜ ሂደት የህዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚችል ሃሳብ የያዘ ፓርቲ እንደመሆነ መጠን ህዝብን ሊያሻግር የሚችል የአመራር ቁመና በመላበስ ለብልፅግና ጉዞ መትጋት እንደሚገባ አንስተዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.