Fana: At a Speed of Life!

ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከእነ ተሽከርካሪዎቹ መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የተለያዩ አልባሳት፣ የሺሻ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዓይነት ሲጋራዎች እና ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን ጭነው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ ነው ተሽከርካሪዎቹ የተያዙት፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እና የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በጋራ ባደረጉት ፍተሻ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ከእነ ተሽከርካሪዎቹ መያዛቸው ታውቋል።

በወንጀሉ የተሳተፋ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ለጉምሩክ ኮሚሽን በደረሰኝ ገቢ መደረጋቸውም ተጠቅሷል።

የፀጥታ ተቋማቱ ኅብረተሰቡ ላደረገው ትብብር አመስግነው÷ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.