Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሕንድ በቡና ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)
በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ጋር ተወይይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ኢትዮጵያ እና ሕንድ በቡና እና ሻይ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ሕንድ ረጅም ጊዜ የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው እና በበርካታ ጉዳዮችም በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በቡና እና ሻይ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የሕንድ ባለሃብቶች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እና በጋራ የተጠናከሩ ስራዎች በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መምከራቸው ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ሽሪ ሮበርት÷ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚገኘውን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንም የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.