በሀገር አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሐሳብ ውድድር የ350 ሺህ ዶላር ሽልማት አሸናፊዎች ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሐሳብ ውድድር የ350 ሺህ ዶላር ሽልማት አሸናፊዎች ተለዩ፡፡
የብሩህ ኢትዮጵያ 2015 የሥራ ዕድል ፈጠራ ሐሳቦች ውድድር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
ውድድሩ በሦስት ዙሮች ተከፍሎ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም በየደረጃው ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ 50 ምርጥ ሐሳቦች ተለይተዋል፡፡
በዚሁ መሠረት እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ዶላር በድምሩ 350 ሺህ ዶላር ተሸልመዋል፡፡
ለቀጣይ ሦስት ወራት የንግድ ልማት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተመላክቷል፡፡
በመራኦል ከድር