Fana: At a Speed of Life!

የጤና አገልግሎትን ተደራሽ የሚያደርግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት በስፋት እየተሰራ ነው -ወ/ሮ ሁሪያ አሊ 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና አገልግሎትን ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ገለጹ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የጤና ዐውደ-ርዕይ ጎብኝተዋል።

ወ/ሮ ሁሪያ አሊ÷ የ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የጤናውን ዘርፍ ጨምሮ በሁሉም መስኮች በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በጤናው የምርምር ዘርፍ የዲጂታል የአሰራር ሥርዓትን ለማጠናከር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በጤናው ዘርፍ ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የአሰራር ስርዓትን በስፋት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ከውጭ የሚገቡ የሕክምና ማሽኖችን በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬ ማዳን የሚያስችሉ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰዎችን የኑሮ ዘይቤ መለወጥ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች እየበለጸጉ መሆኑን ጠቅሰው÷ የጤና አገልግሎትን ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት በስፋት እየተከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።

በጤና ዘርፍ የዲጂታል መተግበሪያዎችና ፖርታሎችን በማልማት ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.