Fana: At a Speed of Life!

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶላት ስነ-ስርዓት በሠላም ተጠናቅቋል- የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶላት ስነ-ስርዓት በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይል አስታውቋል።

የሶላት ሥነ-ሥርዓቱ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ግብረ ሃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት መከበሩንም አስታውቋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ስነ-ስርዓቱ በሠላም እንዲጠናቀቅ ከመላው የከተማዋ ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ላበረከተው አስተዋፅኦ ግብረ-ሃይሉ ማመስገኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.