ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በአውሮፓ ኅብረት የግጭትና ቀውስ ማኔጅመንት ኮሚሽነር ጃንዜል ሌናርሲክ ጋር በቀጣናው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ የቀጣናው የሰብዓዊ እና የምግብ ዋስትና፣ ድርቅ ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭት ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
አውሮፓ ኀብረት በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ እያበረከተ ላለው አስተዋፅኦ ዋና ጸሐፊው አመስግነዋል፡፡