Fana: At a Speed of Life!

የጊኒ ቢሳው ጠቅላይ ሚኒስትር የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጊኒ ቢሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ኑኖ ጎሜዝ ናቢያም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኑኖ ጎሜዝ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውም የጊኒ ቢሳው የጤና ሚኒስትር አረጋግጧል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቦቼ ካንዴና እና ሁለት ሌሎች ሚኒስትሮችም በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።

ጊኒ ቢሳው ኋላቀር የጤና አጠባበቅ ስርዓትና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ያለባት አገር መሆኗን ዘገባው አስፍሯል።

በሀገሪቱ እስካሁን ባለው መረጃ 205 ሰወች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ፤ አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.