በካናዳ ቶሮንቶ የሐረሪ የባሕል እና ስፖርት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ የባሕል እና ስፖርት ፌስቲቫል በካናዳ ቶሮንቶ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተገኝተዋል፡፡
አቶ ኦርዲን በድሪ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ፌስቲቫሉ ዳያስፖራው ከሀገሩ እና ከሕዝቡ ጋር ያለውን ትሥሥር ያጠናክራል ብለዋል፡፡
ዳያስፖራው ማንነቱን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፍ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ርዕሠ-መስተዳድሩ ÷ በቀጣይ ከዳያስፖራው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች የውይይት መድረኮችን ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
በካናዳ ቶሮንቶ ከሚገኘው የአካባቢው ማኅብረሰብ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልና መስተንግዶም ምሥጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡