Fana: At a Speed of Life!

በተፈጥሮ አደጋ የሚጎዱ ወገኖችን ለማገዝ የ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ሥምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ለተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ በተመረጡ ወረዳዎች በተፈጥሮ አደጋ የሚጎዱ ወገኖችን ለማገዝ የ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ሥምምነት ተፈረመ።

ሥምምነቱ ኅብረተሰቡ የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቋቋም ወደ ቀድሞ ሕይወቱ እንዲመለስ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቋል።

የፕሮጀክቱ ዋነኛ ግቦች በተጠቀሱት አካባቢዎች በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተፈናቃይ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ድጋፉ መንግስት አሥፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብና ምላሽ ለመስጠት ያስችለዋልም ነው የተባለው፡፡

ተፈናቃይ ዜጎች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ብሎም ኑሯቸውን በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡

እስካሁን እየተደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ ረገድም አስተዋፅዖ ማበርከቱ ተመልክቷል፡፡

የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮጀክት ሥምምነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ፣ በግብርና ሚኒስቴር እና በተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ አና እርሻ ድርጅት መካከል ተፈርሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.