በአማራ ክልል የፊታችን ሐምሌ 11 ከ260 ሚሊየን በላይ ቸግኞች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የፊታችን ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከ260 ሚሊየን በላይ ቸግኞች በአንድ ጀምበር እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምሕረት ÷ በደቡብ ጎንደር ፣ ምዕራብ ጎጃም ፣ ምዕራብ ጎንደር ዞኖች እና ደሴ ከተማ አስተዳደር ምዕራፍ ሁለት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ተጀምሯል ብለዋል፡፡
እስካሁንም ግማሽ ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡
በክረምቱ ወቅትም እንደክልል 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን አመላክተዋል፡፡
በታለ ማሞ