Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን የማህበራዊና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመሥጠት እየተሰራ ነው – ከንቲባ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የዜጎችን የማህበራዊና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ምላሽ ለመሥጠት ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ፡፡

“ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር የታክስ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ መድረክ የመክፈቻ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው ፡፡

አቶ ከድር ጁሃር በዚሁ ጊዜ እንዳሉት መንግስት የዜጎችን የማህበራዊና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመሥጠት ዘርፈ ብዙ ዕቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የአስተዳደሩን ገቢ ለመጨመር በተሰሩ ስራዎች ውጤት መገኘቱንና በዚህም በበጀት ዓመቱ ያለፉት 11 ወራት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ መሠብሰብ መቻሉን አንስተዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር የታስክ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ በበኩላቸው፥ የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት የታስክ ስርአቱን በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ ገቢን በአግባቡ መሠብሠብ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው የታክስ ንቅናቄም የአስተዳደሩን ግብር የመሰብሰብ አቅም እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

በነስሪ ዩሱፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.