Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

ፎረሙ እየተከናወነ የሚገኘው “በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያ የስራ ፈጠራ፣ የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

የአፍሪካ የስራ እድል ፈጠራ ፎረም አካል የሆነው የአፍሪካ ትስስር ቀንም በመከበር ላይ ይገኛል።

በፎረሙ ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣የአፍሪካ ሕብረት የንግድ፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሞኒክ ንሳንዛባንጋዋ እና የአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ተቋማት አመራሮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፎረሙ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን ተግበራ፣ በአፍሪካ ወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ እና የአፍሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ጥምረት ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፎረሙ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ የስራ እድል ፈጠራ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የጎንዮሽ እና የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.