Fana: At a Speed of Life!

እስከ ሐምሌ 23 ድረስ ከ3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ተጨማሪ ማዳበሪያ ከውጭ እንደሚጓጓዝ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ፊታችን ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ከ3 ሚሊየን 685 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ ማዳበሪያ ከውጭ እንደሚጓጓዝ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

እስከ ሐምሌ 23 ከውጭ ከሚጓጓዘው ውስጥ÷ 2 ሚሊየን 485 ሺህ ኩንታል ዩሪያ፣ 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እና 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን መሆናቸው ተብራርቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከገዛው 15 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ÷ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ 10 ሚሊየን 275 ሺህ 320 ኩንታል ከውጭ መጓጓዙ ተገልጿል፡፡

በትናንትናው ዕለትም 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 8 ሚሊየን 487 ሺህ 429 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች እየተሰራጨ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.