Fana: At a Speed of Life!

የባለጣዕሙ ቅርንፉድ ጥቅም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅርንፉድ ሁለገብና ጣዕምን የሚጨምር ጠቃሚ ቅመም ነው፡፡

ቅርንፉድ ፋይበር፣ ቫይታሚን እና ጠቃሚ ማዕድኖችን የያዘ ቅመም ሲሆን፥ ምግብ ላይ ጣዕም ከመጨመሩም በላይ ካንሰርን ጨምሮ በሽታን በመከላከል ለጤና ጠቃሚ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቅርንፉድ ውስጥ የሚገኙት ውህዶች ካንሰርን ለመከላከል ይረዳሉ፤ በዚህም የእጢን እድገት ይገታል ይባልለታል፡፡

ሆኖም ይህ ጥናት ተጨማሪ ማረጋገጫዎች እንደሚያስፈልጉት ተጠቁሟል፡፡

ቅርንፉድ የፀረ-ተህዋሲያን ባህሪ ያለው መሆኑ እንደ ባክቴሪያ ያሉ ረቂቅ ተሕዋስያንን እድገት ለማስቆም ይረዳል።

በዚህም የምግብ መመረዝ የሚያስከትለውን የባክቴሪያ ዓይነት በማስወገድ ጤናዎ ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያግዝም ነው፡፡

በተጨማሪም የአፍ ጤናን በመጠበቅ ከአፍ ጤንነት መጓደል ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ይጠብቃል፡፡

እንዲሁም ቅርንፉድ የጉበት ጤናን ይጠብቃል፤ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቅርንፉድ ውስጥ የሚገኙት ጠቃሚ ውህዶች የጉበት ጤናን ለማሻሻል ስለሚረዱ ሐኪምን በማማከር መጠቀም ይቻላል።

ቅርንፉድ የደም ስኳር መጠንን ለማስተካከል ሊረዳ እንደሚችልም የተጠቀሰ ሲሆን ፥ የኢንሱሊን የመመረት አቅምን የሚጨምርና የደም ስኳር መጠንን በመቀነስ የሰው ልጅ ጤና እንዲጠበቅ እንደሚያደርግ ከኽልዝላይን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.