የሶማሌ ክልል የ2016 በጀት ከ38 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2016 በጀት 38 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ ማሳለፉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡
የክልሉ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የ2016 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት 38 ቢሊየን 395 ሚሊየን 984 ሺህ 793 ሚሊየን ብር እንዲሆን የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ አፅደቋል።
ካቢኔው በቀረበለት ረቂቅ የበጀት ውሳኔ ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ወደ ክልሉ ምክር ቤት መርቷል።
በክልሉ በ2016 ዓ.ም 16 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን የክልሉን በጀት በቀጣይ 43 በመቶ ከገቢው ለመሸፈን ወደ ስራ ተገብቷል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።