Fana: At a Speed of Life!

የቁልቢ ገብርኤል ክብረ-በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መጠናቀቁን ግብረ ኃይሉ አስታወቀ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቁልቢ ገብርኤል ክብረ-በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ÷ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ክብረ-በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅት አድርገው  ወደ ተግባር መግባታቸውን  ገአስታውቋል፡፡

የጋራ ግብረ-ኃይሉ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ እና በምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች ሰላምና ደኅንነት እያስከበረ መቆየቱንና  አሁን ላይ የአካባቢው ሰላም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአካባቢው የፀጥታውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር በሁሉም አቅጣጫ አስፈላጊውን ጥበቃና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ሕግን አክብረው በማሽከር የበዓሉ ታዳሚዎች ያለ ምንም የትራፊክ አደጋ በዓሉን በሰላም አክብረው  እንዲመልሱ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግብረ-ኃይሉ አሳስቧል።

የአካባቢው ሕብረተሰብ ለሰላምና ደኅንነት ስጋት የሆኑ ነገሮችን ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.