የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ አመራሮች የጤና ኤግዚብሽንን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘውን አገር አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽንን ጎብኝተዋል።
አመራሮቹ የጤናውን ዘርፍ ከማዘመንና ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ከመስጠት ረገድ ሀገሪቱ የደረሰችበት ደረጃ መመልከት መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
በተለይ የአገርበቀል የህክምና እውቀትን ለማዘመን እና በየደረጃው የሚገኘውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እንደሀገር እየተሰራ ያለዉን ስራ ጥሩ አድርጎ ያሳያልም ነው ያሉት።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በነበረው ግጭት የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ከመገንባት፣ ከማጠናከርና በሙሉ አቅም ወደ ስራ ከማስገባት ረገድ እየተሰራ ያለው ስራ መልካም ቢሆንም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡