ሚኒስቴሩ ከተመድ የፕሮጀክት አገልግሎቶች ጽ/ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተመድ የፕሮጀክት አገልግሎቶች ጽሕፈት ቤት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከተመድ የፕሮጀክት አገልግሎቶች ጽ/ ቤት በኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ስምምቱ ሁለቱ ተቋማት በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የትብብር ማዕቀፍ ይበልጥ ለማስፋት እና ለማጠናከር ያግዛል ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሁለቱ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጡ እንደሚያስችል መገለጹን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ ያመላክታል።