Fana: At a Speed of Life!

ከ389 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ389 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከሐምሌ 7 እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ባደረገው ክትትል 187 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እንደያዘ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከ201 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሲይዝ ፥ በድምሩ ከ389 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙንም ነው ያስታወቀው።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም መመዝገቡም ነው የተመላከተው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ባደረጉት ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸው ተገልጿል።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 10 ግለሰቦች እና 10 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.