Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ለሚገነባው ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ጥራትን በፍትሃዊነት ለማዳረስ እየተሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሶማሌ ክልል ፋፋን ዞን ባቢሌ ወረዳ ኦቦሻ ቀበሌ ውስጥ ለሚገነባው የኦቦሻ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ትምህርት ቤቱ የሚገነባው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የትምህርት ጥራትን በፍትሐዊነት ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ኀገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ ድርጅቱ በተቀመጠለት ጊዜ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ በቀጣይ አምስት ዓመታት ከሚገነቡ 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 16ቱ በመንግስት እንደሚገነቡ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.